(Translated by https://www.hiragana.jp/)
ውክፔዲያ - ማፑቶ Jump to content

ማፑቶ

ከውክፔዲያ

ማፑቶ (በፖርቱጋልኛ: Maputo) የሞዛምቢክ ዋና ከተማ ነው።

ማፑቶ

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1998 ዓ.ም.) የአካባቢውን ኗሪ ሲጨመር 1,800,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,200,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 25°58′ ደቡብ ኬክሮስ እና 32°35′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ፖርቱጊዙ ዠብደኛ ሉሬንሶ ማርኬስ ዙሪያውን በ1536 ዓ.ም. በመርከብ ተጓዘ። በ1868 ዓ.ም. (1876 እ.ኤ.አ.) ከተማው ተመሰርቶ ስሙ እሱን ለማክበር ሎሬንሶ ማርኬስ ሆነ። በ1890 ዓ.ም. የቅኝ አገሩ መቀመጫ ሆነ። ዳሩ ግን ሞዛምቢክ ነጻ ከወጣ በኋላ፣ ስሙ በ1968 ዓ.ም. ወደ ማፑቶ ተለወጠ።