(Translated by https://www.hiragana.jp/)
ውክፔዲያ - ካነፈሬ 4 ሶበክሆተፕ Jump to content

ካነፈሬ 4 ሶበክሆተፕ

ከውክፔዲያ

==

ካነፈሬ ሶበክሆተፕ
የካነፈሬ ምስል
የካነፈሬ ምስል
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1690-1684 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ 1 ነፈርሆተፕ
ተከታይ መርሆተፕሬ 5 ሶበክሆተፕ
ባለቤት ጫን
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት ሀዓንኸፍ

==


ካነፈሬ 4 ሶበክሆተፕ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1690 እስከ 1684 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የወንድሙ የ1 ነፈርሆተፕ ተከታይ ነበረ።

አባቱ ሀዓንኸፍና እናቱ ከሚ ነበሩ፤ የዚህም ሀዓንኸፍ አባት ነሂ እናቱም ሰነብቲሲ ተባሉ። ይህም ነሂ «የከተማ ሻለቃ» የሚመስል ማዕረግ እንደ ነበረው ይታወቃል። የሀዓንኸፍ ፫ ልጆች ሁሉም ፈርዖኖች ስለ ሆኑ በበርካታ ጽላቶች ይከበራል።

ወደ ነፈርሆተፕ ዘመን መጨረሻ ወንድሙ ሲሐጦር ከእርሱ ጋራ የጋርዮሽ ፈርዖን ተደርጎ ሲሐጦር በጥቂት ወራት ውስጥ እንደ ሞተ ይመስላል፤ ከዚያም ሌላ ወንድማቸው ካነፈሬ 4 ሶበክሆተፕ የጋርዮሽ ፈርዖን ሆነ። ከዚያም ትንሽ በኋላ ነፈርሆተፕ ዓርፎ ካነፍሬ ሶበክሆተፕ ለብቻ ፈርዖን ሆነ። ከአንዳንድ ቅርስ ይታወቃል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነፈርካሬ ኢይመሩ ሲሆን በጅሮንዱ ሰነቢ ተባለ፣ ከፍተኛ ሎሌውም ነባንኽ ይታወቅል። ንግሥቱ ጫን ነበረች።

የካነፍሬ ተከታይ መርሆተፕሬ 5 ሶበክሆተፕ እንደ ሆነ ይታሥባል።

ቀዳሚው
1 ነፈርሆተፕ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን ተከታይ
መርሆተፕሬ 5 ሶበክሆተፕ
  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)