(Translated by https://www.hiragana.jp/)
ውክፔዲያ - የባንቱ ፍልሰት Jump to content

የባንቱ ፍልሰት

ከውክፔዲያ

የባንቱ ፍልሰት የመጀመሪያውን የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሕዝቦች ከዛሬዎቹ ካሜሩን እና ናይጄሪያ በአንድ ሺህ ዓመታት ጊዜ ውስጥ ያደረጉት ፍልሰት ነበር። በአቅራቢያቸው ከሚገኙት ሕዝቦች ጋር ቋንቋና ዕውቀት በመለዋወጥ አዳዲስ ኅብረተሰቦችን ፈጥረዋል። ፍልሰቱ የተጀመረው ግብርና ከተጀመረ በኋላ እንደሆነ የሚታመን ሲሆን በመጀመሪያ ወደ ምሥራቅ ከዚያም ወደ ደቡብ አቅጣጫ አምርቷል።